በአይሲቲ ዘርፍ ላይ በመሠማራት ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ድርጅቶች ጋር እየሠራ የሚገኘው ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር፤ በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ በጅግጅጋ ከተማ የስማርት ሲቲ ዕቅዶች
ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ በጅግጅጋ ከተማ የስማርት ሲቲ ዕቅዶች ትግበራ ላይ ከመስተዳድሩ ጋር ውይይት አካሔደ
በአይሲቲ ዘርፍ ላይ በመሠማራት ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ድርጅቶች ጋር እየሠራ የሚገኘው ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር፤ በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ በጅግጅጋ ከተማ የስማርት ሲቲ ዕቅዶች ትግበራ ላይ ከመስተዳድሩ ጋር ውይይት አካሔዷል። የድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ውይይቱን ያካሔዱት ከሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ጋር ነው።
የድርጅቱ ኃላፊዎች ከምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ በጅግጅጋ እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እና የመሠረተ ልማት ሥራ የስማርት ሲቲ ፕሮግራሞችን መሠረት በማድረግ ከተማውን በማዘመን ከኋላ ቀር አሠራር ለመውጣት የሚያስችሉ የስማርት ሲቲ መርሃ ግብሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ከመግባባት ላይ ተደርሷል።
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አቶ ኢብራሂም ዑስማን በድሬዳዋ ላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ከተማውን የስማርት ስቲ እቅዶችን ተግባራዊ ካደረገው ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ ጋር መርሐ ግብሩን በጅግጅጋ ተግባራዊ ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን አረጋግጧል።
ስካይ ሊንክ ቴክኖሎጂስ ላለፉት ዓመታት በተለይ በሶፍትዌር፣ የኔትወርክ እና ሴኪውሪቲ ኢንፍራሰትራክቸር ጋር ተዛማጅ ሥራዎችን በመሥራት የሚታወቅ ነው። በአሁኑ ሰዓት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ጋር በስማርቲ ሲቲ ፕሮጀክት ላይ እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።